የቅዱሳን ሕይወት

 

ቅዱስ ፉልቪያን-ማቴዎስ (St. Fulvian-Matthew) ኢትዮጵያ ንጉስ

ከሀዋርያውና ወንጌላዊው ማቴዎስ የህይወት ታሪክ

 

 

ቅዱሱ ሐዋርያ የክርስቶስን ወንጌል ወደ ሲሪያ፣ ሜዲያ፣ ፐርያ፣ ፓቲያ በመጨረሻም ስብከቱን ኢትዮጵያ ውስጥ ሰማዕት ሆኖ ጨረሰ፡፡ ቅዱስ ሀዋርያ ማቴዎስ የተወሰኑ ጣዖት አምላኪዎችን ወደ ክርስቶስ እምነት ቀይሯቸዋል፡፡ ቤተክርስቲያን አጊኝቶ ሚርሜና ከተማ ውስጥ ቤተ-መቅደስ ሰራና አጋሩን ፕላቶን ቄስ አድርጎ ሾመው፡፡

ቅዱሱ ሐዋርያ ከኢትዮጵያውያን ጋር እንዲያወራ እግዚብሄርን አጥብቆ ሲለምነው፣ ራሱ ጌታ በወጣት ተመስሎ እሱ ጋር መጣ፡፡ ዱላም ሰጠው፤ በቤተ-ክርስቲያኑ ደጃፍም እንዲተክለው አዘዘው፡፡ ጌታመ ዛፍ ክሱ ያድጋለ፣ ፍሬም ያፈራል ከስሮቹም ውሃ ይፈልቃል፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ በምንጩ ሲታጠቡና  ፍሬውንም ሲበሉ የእብደት መንገዳቸውን ትተው ጨዋና ጥሩ ሆኑ፡፡

ቅዱስ ሐዋርያ ዱላውን ወደ ቤት ክርስቲያኑ ይዞ እየመጣ እያለ መንገድ ላይ ከመሬቱ ገዢ (ፉልቪያን) ልጅና ሚስት (ቅድስር ኢፊጌንያ - St. Iphigenia) ጋር ተገጣጠመ፡፡ በክርስቶስ ስም ቅዱሰ ሐዋርው አዳናቸው፡፡ይህ ታአምር በብዙ ቁጥር የሚጠጉ አረመኔዎችን ወደ ጌታ ለወጣቸው፡፡ ነገር ግን ገዢው ሰዎቹ ክርስቲያን እንዲሆኑና ጣኦት ማምለካቸውን እንዲያቆሙ አልፈለገም፡፡ ሐዋርያውን በጥንቆላ ወንጅሎ እንዲገደል ትእዛዝ አስተላለፈ፡፡

የቅዱስ ማቴዎስን ጭንቅላት ወደታች አቅዝቀው እንጨት ደረቡበትና አቃጠሉት፡፡ እሳቱ ሲነበለነል ሁሉም ሰው እሳቱ ማቴዎስን እንዳልጎዳው አየ፡፡ ከዛም ፉልቪያን ተጨማሪ እንጨት እንዲጨመር አዘዘ፤ በድፍረትም ተሞለቶ 12 ጣኦቶች በእሳቱ ዙሪያ እንዲደረደሩ አዘዘ፡፡ ግን እሳቱ ጣኦቶቹን አቀለጠ፤ ወደ ፉለቪያንም ቦግ አለ፡፡ የደነገጡት ኢትዮጵያውያንም ወደ ቅዱሱ በመዞር ምህረትን ለመኑ እናም በሰማእቱ ጸሎት እሳቱ ጠፋ፡፡ የቅዱስ ሐዋርያውም ሰውነት ምንም ጉዳት ሳይደርስበት ወደ ጌታ ሄደ፡፡

ገዢው ፉለቪያን ስለተግባሩ በጣም ተጸጸተ፤ አሁንም ግን ጥርጣሬ ነበረው፡፡ በራሱ ትእዛዝም የቅዱስ ማቴዎስንም አስከሬኑን በብረት ሬሳ ሳጥን ውስጥ አስገብተው ወደባህር ወረወሩት፡፡ ይህን ሲያደርግ ፉቪያን ˮየማቴዎስ አምላክ የሐዋርያውን ሰውነት ምንም ሳይቀየር በእሳቱ እንዳቆየው በውሃም ካቆየው ይህ አንዱን እውነተኛ አምላክ ለማምለክ ተገቢ ምክንያት ይሆናልˮ ብሎ ተናገረ፡፡

ያን ምሽትም ሐዋርያው ማቴዎስም በቅስ ፕላቶን ህልም ውስጥ ተገለጠ እናም ሬሳውን ለመፈለግ ከካህናት ጋር ወደባህሩ ዳርቻ እንዲሄዱ አዘዘው፡፡ ጻድቁ ፉልቪያን እና የክብር ተከታዮቹ ከቅሱ ጋረ ወደ ባህር ዳርቻው ሄዱ፡፡ የሬሳ ሳጥኑም በማእበል ተሸክሞ ወደ ሐዋርያው ወደሰራው ቤተ-ክርስቲያን ተወሰደ፡፡ ከዛም ፉልቪያን ቅዱስ ሐዋርያ ማቴዎስን ይቅርታ ለምኖ ቄስ ፕላቶነ አጠመቁት፤ የአምላክ ትእዛዝንም በመታዘዝ ማቴዎስ የሚል ስምም ሰጡት፡፡ 

በቅርቡም ግዛቱን ትቶ ቀሲስ ሆነ፡፡ በቄስ ፕላቶን ሞት ጊዜም ሐዋርያው ማቴዎስ ተገልጠው ወደኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን እንዲሄድ አሳሰቡት፡፡ ቄስ ከሆኑ በኋላ ቅዱስ ፉለቪያን ማቴዎስ የመንግስተ ሰማያትን በጎ ስራ በመቀጠል የእግዚአብሄርን ቃል በመስበክ ታተረ፡፡

 

            

                                                    

                                                  ዝግጅት በ: ሃ. ጎ. ፣ ሮ. ኢ.