የቅዱስ ጳውሎስ አስተምህሮዎች ምርጫ መግቢያ
በዚህ
የሚገኙት የጥቅስ ስብስቦች የተወሰዱት በቅዱስ ጳውሎስ ከተጻፉት አሥራ አራቱ መልእክታት ነው፡፡ ጥቅሶቹ
የተወሰዱበትን የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ለማግኘት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ፡
https://www.wordproject.org/bibles/am/
እነዚህ የጥቅስ ስብስቦች የተመረጡበት ዋናው ምክንያት አንዲት፣ ቅድስት፣ ኵላዊት እና ሐዋርያዊት የሆነችው
ቤተክርስቲያን ምዕመናን በሕይወታቸው ውስጥ እንዲተገብሩ የምታስተምራቸውን ዋና ዋና ትምህርቶች የያዙ በመሆናቸው
ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ያስተላለፉልንን ሐዋርያት ትምህርት ማጥናቱም አስፈላጊ ከመሆኑ ባሻገር ኦርቶዶክሳዊ
ጭምር መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም የእግዚአብሔርን ቃል በምናነብበት ወቅትም የምናነበው ቃል በሕይወታችን
ውስጥ እንዴት ማስረጽ እና መተግበር እንደሚኖርብን አውቀን በመንፈስ ራሳችንን ማነጽ ይገባል፡፡ ሆኖም ግን
በቤተክርስቲያን ሊቃውንት እና በቅዱሳን እሳቤ በኩል በሚገባ የተገለጸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሲነበብ ዘውትር
በቤተክርስቲያን የትርጓሜ መነጽር በኩል መሆኑን ልብ ማለት ይኖርብናል፡፡ ይህንን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እና
አንባቢው የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆን በማሰብ አንዳንዶቹን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በአማርኛው ወይም በእንግሊዝኛው
OODE [ኦርቶዶክሳዊ ትምህርተ ዶግማ መድረክ]ከሚገኙና ጥልቅ ትንታኔ ካለባቸው ጽሑፎች ጋር አያይዘናቸዋል፡፡
ለወደፊቱም ተጨማሪ ማብራሪያዎችን በማያያዝ መድረኩን ለማዳበር ተስፋ አለን፡፡
ጥቅሶቹን
በምታነቡበት ወቅት ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ካላችሁ
AmharicOODE@gmail.comበሚለው አድራሻችን ልትጽፉልን ትችላላችሁ፡፡
|